የመስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
Listen now
Description
የሶማሊያና የግብጽ ፕሬዝደንቶች በኤርትራ ይፋዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው። የሁለት ሃገራት መሪዎች ከኤርትራው ፕሬዝደንት ጋር በሁለትዮሽ፤ በአፍሪቃ ቀንድና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ተገልጿል። የተመድ በመላው ዓለም ወጣቶች ለዘርፈ ብዙ ጥቃቶች መጋለጣቸውን አመለከተ። የተመድ ታይቶ ለማይታወቅ የጥቃት ማዕበል እና ጦርነት ባመጣው ጾታዊ ጥቃት እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ፤ ረሃብና መፈናቀል ተጋልጠዋል። ግብጽ በሱዳን ጦርነት በአየር ድብደባ ተሳትፋለች በሚል ከፈጥኖ ደራሹ ኃይል መሪ የቀረበባትን ክስ አስተባበለች። የጎርጎሪዮሳዊው ዓመት 2024 የስነጽሑፍ የኖቤል ሽልማት ለደቡብ ኮርያዋ ደራሲ ሃን ካን ተሰጠ።
More Episodes
-የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2017 ዓመት 582 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አጠደቀ።የምክር ቤት አባላት ተጨማሪዉ በጀት የዋጋ ግሽበትን ያጠናክራል፣ ግብር ከፋዩን ያማርራል፤ ምጣኔ ሐብቱን ያዉካል የሚል ተቃዉሞ አንስተዉ ነበር ግን በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።-የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ 3 የመብት ተሟጋች ድርጅቶችን ማገዱን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ተቃወመዉ፤ አምንስቲ ኢንተርናሽናል አወገዘዉ።-እስራኤልና የሊባኖሱ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሒዝቡላሕ...
Published 11/26/24
Published 11/26/24
አርስተ ዜና --«G7» ሰባቱ በኢንዱስትሪ የበለፀጉት አገራት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በመካከለኛዉ ምስራቅና በሩስያ ዩክሬይን ቀዉስ ጉዳይ ላይ ለመምከር የሁለት ቀን ስብሰባ ጣልያን ዉስጥ ጀመሩ። ሚኒስትሮቹ በእስራኤል ባለስልጣናትና በሃማዝ ወታደራዊ አዛዥ ላይ የተላለፈዉ የእስር ማዘዣም የመወያያ ርዕሳቸዉ ነዉ።--“ፅንፈኛና ሽብርተኛ” ያላቸው አካላት ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ፈጸሙት ያለውን ግድያ፤ የአማራ ከልል መንግሥት አወገዘ፡፡ ያም ሆኖ፤...
Published 11/25/24