Episodes
-የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2017 ዓመት 582 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አጠደቀ።የምክር ቤት አባላት ተጨማሪዉ በጀት የዋጋ ግሽበትን ያጠናክራል፣ ግብር ከፋዩን ያማርራል፤ ምጣኔ ሐብቱን ያዉካል የሚል ተቃዉሞ አንስተዉ ነበር ግን በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።-የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ 3 የመብት ተሟጋች ድርጅቶችን ማገዱን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ተቃወመዉ፤ አምንስቲ ኢንተርናሽናል አወገዘዉ።-እስራኤልና የሊባኖሱ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሒዝቡላሕ ተኩስ ሊያቆሙ ነዉ።
Published 11/26/24
Published 11/26/24
አርስተ ዜና --«G7» ሰባቱ በኢንዱስትሪ የበለፀጉት አገራት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በመካከለኛዉ ምስራቅና በሩስያ ዩክሬይን ቀዉስ ጉዳይ ላይ ለመምከር የሁለት ቀን ስብሰባ ጣልያን ዉስጥ ጀመሩ። ሚኒስትሮቹ በእስራኤል ባለስልጣናትና በሃማዝ ወታደራዊ አዛዥ ላይ የተላለፈዉ የእስር ማዘዣም የመወያያ ርዕሳቸዉ ነዉ።--“ፅንፈኛና ሽብርተኛ” ያላቸው አካላት ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ፈጸሙት ያለውን ግድያ፤ የአማራ ከልል መንግሥት አወገዘ፡፡ ያም ሆኖ፤ የሰሞኑን ግድያ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ በተለያዩ ወገኖች ጥሪ እየቀረበ ነው። -- ቀሲስ በላይ መኮንን ዛሬ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ማሰማት ጀመሩ፡፡
Published 11/25/24
የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ የሕግ ኮሚቴ በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል እና አጥፊዎችን ለመቅጣት የሚያስችል ሥምምነት ለማዘጋጀት የሚያስችል ድርድር እንዲጀመር መንገድ የሚጠርግ የውሳኔ ሐሳብ አጸደቀ። በቀድሞው የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ከጸጥታ ሹማምንቶቻቸው ጋር አስቸኳይ ስብሰባ አካሔዱ። እስራኤል በቤይሩት እና ሾምስታር በተባለች ከተማ በፈጸመቻቸው ሁለት ጥቃቶች ቢያንስ 19 ሰዎች መገደላቸውን ሊባኖስ አስታወቀች። የከባቢ አየር ለውጥ የበረታ ዳፋ የሚያሳድርባቸው ትናንሽ የደሴት ሀገራት እና አፍሪካውያን በአዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ በመካሔድ ላይ ከሚገኘው ድርድር ረግጠው በመውጣት ተቃውሟቸውን አሰሙ።
Published 11/23/24
አርስተ ዜና፤ --በአዘርባጃን ባኩ እየተካሄደ ባለዉ የመጨረሻ ቀን የአየር ንብረት ጉባዔ ሁለተኛው የዕቅድ ስምምነት ለመጀመሪያ ጊዜ ወሳኝ የአየር ንብረት የፋይናንስ ግብ ማሳያ ቁጥር ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።--እስራኤል እና አጋሮችዋ ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፤ የእስር ማዘዣ እንዲሰጥ መወሰኑን አወገዙ። በሌላ በኩል ቱርክና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እርምጃውን በደስታ ተቀብለውታል።--የሃድያ ዞን ፖሊስ በሙስና ተጠርጥረው የተያዙ አንድ ከፍተኛ የዞን ባለሥልጣንን፤ ሆን ብለው ከማረሚያ ቤት አስምልጠዋል ያላቸውን፤ አምስት የፖሊስ አባላትን አሠረ፡፡
Published 11/22/24
የኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለ2017 ተጨማሪ 582 ቢሊዮን ብር ገደማ በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲቀርብ ወሰነ። የቀድሞው የትግራይ ኃይሎች አባላት የነበሩ ከ300 በላይ ተዋጊዎች የጦር መሣሪያዎቻቸውን ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አስረከቡ። ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ኬንያ ከሕንዱ አዳኒ ግሩፕ ጋር የናይሮቢ የአውሮፕላን ማረፊያን ለማስፋፋት እና የኃይል መሠረተ-ልማት ለመገንባት የያዘችውን ዕቅድ ሰረዙ። ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀሎች መዳኛ ፍርድ ቤት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ፣ የቀድሞ መከላከያ ሚኒስትራቸው ዮቭ ጋላንት እና የሐማስ ወታደራዊ አዛዥ ሞሐመድ ዲይፍ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣ።
Published 11/21/24
የኅዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ትጥቅ የፈቱ፣ የሰላም ስምምነት የፈረሙ ድርጅቶች ውስጥ አባል የነበሩ እና በ6 ክልሎች የሚገኙ 371,971 የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት ወደ ተሃድሶ ማዕከላት እንደሚገቡ ተናግሯል። ማዕከላዊ ሱዳን ውስጥ ፈጥኖ ደራሹ ኃይል ከትናንት አንስቶ ባደረሰው ጥቃት 40 ሰዎች መገደላቸው ተሰማሩ። በአዘርባጃኑ ኮፕ 29 ላይ የተሳተፉ 25 ሀገራት አዳዲስ የድንጋይ ከሰል የኃይል ማመንጫ ላለመገንባት ቃል ገቡ።ቃል ከገቡት ባለጸጋ ሀገራት መክከል ብሪታንያ ፣ ካናዳ ፣ፈረንሳይ፣ ጀርመን እና አውስትራሊያ ይገኙበታል።
Published 11/20/24
አርዕስተ ዜና *የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ጉባኤው የአንድ የምክር ቤቱን አባል የአለመከሰስ መብት አነሳ ። *የሶማሊላንድ ፕሬዚደንት ሙሴ ቢሂ አብዲ በፕሬዚደንታዊ ምርጫው ተሸነፉ ። ራስዋን የሶማሊላንድ ሪፐብሊክ ብላ የምትጠራዉ ግዛት የምርጫ ኮሚሽን ተቃዋሚው አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ በቅጽል ስማቸው «ኢሮ» የፕሬዚደንታዊ ምርጫውን ማሸነፋቸውን ዛሬ ይፋ አድርጓል ። *ሩስያ ዩክሬንን በጦር ኃይል ከወረረች ከ1000 ቀን በኋላ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የዩክሬን ጦር በዩናይትድ ስቴትስ የረዥም ርቀት ሚሳይል ሩስያን መምታቱን ዐሳወቀ ። የ
Published 11/19/24
DW Amharic አርስተ ዜና፤ --የቡድን 20 አገሮች የሁለት ቀናት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ብራዚል ሬዮዴጄኔሮ ላይ ጀመረ። 19 በእንዱስትሪ የበለጽጉ እና ያደጉ የዓለም አገሮች እንዲሁም የአውሮጳ ህብረትን ያካተተዉ የቡድን 20 ጉባዔን ለመሳተፍ ሀገራት መሪዎች ከፍተኛ ልዑካኖቻቸዉን አስከትለዉ በጉባኤዉ ለመሳተፍ ሬዮዴጄኔሮ ገብተዋል። --የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደዓ ዛሬ በቀጠሮያቸው መሰረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀረቡ። --የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይላት በጦርነቱ ለተፈፀመዉ ሰብዓዊ ጥሰት ኃላፊነት እንደማይወስዱ ገለፁ።
Published 11/18/24
በጋምቤላ ክልል ከ4 ዞኖች ለ138 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ። ሳዑዲ አረቢያ በጎርጎሮሳውያኑ 2024 ሰባት ኢትዮጵያውያን ጨምሮ ከ100 በላይ የውጪ ሀገራት ዜጎች በሞት መቅጣቷን AFP ዘገበ። ሒዝቦላሕ ቃል አቀባዩ ሞሐመድ አፊፍ በእስራኤል የአየር ጥቃት መገደላቸውን አስታወቀ። ሩሲያ በ120 ሚሳይሎች እና 90 ሰው አልባ አውሮፕላኖች በዩክሬን የኃይል መሠረተ-ልማቶች ላይ ከባድ የአየር ድብደባ ፈጸመች። የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ ከሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ያደረጉትን የስልክ ንግግር ተከላከሉ። የቻይናው ፕሬዝደንት ሺ ዢንፒንግ ከአሜሪካው ተመራጭ ፕሬዝደንት ዶናልፕ ትራምፕ ጋር ለመሥራት ቃል ገቡ።
Published 11/17/24
ማሊ ውስጥ የቆየው የተመድ ተልዕኮ በዛሬው ዕለት ለሀገሪቱ ወታደራዊ ኹንታ ባለሥልጣናት ወታደራዊ ሰፈሩን አስረከበ። በያዝነው ዓመት ታኅሣስ ማለቂያ አካባቢ ተልዕኮው አጠቃሎ ከማሊ ይወጣል። ዓመታዊው የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ተከታታይ ጉባኤ የተነሳለትን አላማ ማሳካት ተስኖታል የሚሉ ወገኖች የማሳሰቢያ ደብዳቤ ለጉባኤው አቀረቡ። ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የመካከለኛው ምሥራቅ እና የሩሲያ እና የዩክሬን ጦርነት መቆም አለበት አሉ። የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ ከሁለት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ከሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ተነጋገሩ።
Published 11/15/24
የኅዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና ባለፈው ማክሰኞ የክስ ጭብጣቸው በዐቃቤ ሕግ ተሻሽሎ ከቀረበው በሽብር ወንጀል ከተከሰሱ 51 ሰዎች መካከል በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት ዛሬ ሐሙስ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ። በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ በሽብር ወንጀል ክስ ከቀረበባቸው 51 ተከሳሾች መካከል አራት የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ይገኙበታል። የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት፣ የኤርትራ ጦር ከኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት እንዲወጣ በይፋ አለመጠየቁ አሳሳቢ ነው የዓሲምባ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አስታወቀ። ቱርክ ብሪክስ በተባለው ቡድን የአጋርነት ደረጃ ተሰጣት።
Published 11/14/24
-የሶማሊላንድ ሕዝብ የወደፊት ፕሬዝደንቱን ለምረጥ ዛሬ ድምፅ ሲሰጥ ዉሏል።በምርጫዉ ራስዋን የሶማሊላንድ ሪፐብሊክ ብላ የምትጠራዉን ግዛት ላለፉት ሰባት ዓመታት የመሩት ፕሬዝደንት ሙሴ ቢሒ አብዲ ከዋነኛዉ ተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩ ከአብዲረሕማን መሐመድ አብዱላሒ ጋር በቅርብ ርቀት ይፎካከራሉ።----የእስራኤል ጦር ዛሬም እንደመሰንበቻዉ የጋዛ ሠርጥንና የሊባኖስ ርዕሰ ከተማ ቤይሩትን ሲደበድብ ዋለ።--ባኩ-አዘር በጃን በተያዘዉ የዓየር ንብረት ጉባኤ ላይ የአየር ንብረትን በመበከል ቀዳሚዉን ሥፍራ የሚይዙ ሐገራት መሪዎች ባለመገኘታቸዉ ጉባኤዉ ለአግባቢ ዉጤት መድረሱ እያነጋገረ ነዉ።
Published 11/13/24
*አራት የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎችን ጨምሮ በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ በሽብር ወንጀል ክስ የቀረበባቸው 51 ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመስጠት ለሕዳር 5 እንዲቀርቡ ቀጠሮ መስጠቱ ተገለጠ ። ​*የጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን ሥርዓተ-ቀብር ማክሰኞ ኅዳር 03 ቀን፣ 2017 ዓ.ም በእስራኤል ቴል አቪቭ ከተማ ያልሚና ያል ኮን በተባለ ሥፍራ ተፈጸመ ። *በቅርቡ ጥምረቱ የፈረሰበት የጀርመን መንግሥትን ለመተካት ዋነኞቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ ሀገር አቀፍ ምርጫ ለማካሄድ ስምምነት ላይ ደረሱ ።
Published 11/12/24
DW Amharic የሳዑዲ አረቢያዉ ልዑል ማሐመድ ቢን ሰልማን በጋዛ እና በሊባኖስ አፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠየቁ። ቢን ሳልማን ጥሪዉን ያቀረቡት በሳውዲ አረቢያ ሪያድ በአረብ ሊግና በእስልምና ትብብር ድርጅት የጋራ ጉባዔ ላይ ነው።//በኤርትራ ፍርድ ከ 23 ዓመታት በላይ የታሰረዉ ትዉልደ ኤርትራዊዉ ዳዊት ይህሳቅ፤ ለሃሳብ ነጻነት ላደረገዉ ትግል የስዊድንን የመብት ከፍተኛ ሽልማት አገኘ።// ራስ ገዝዋ ሶማሌላንድ የፊታችን ረቡዕ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንደምታካሂድ ተነገረ።// ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከጀርመን ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ ጋር በአውሮጳ "ሰላምን በመመለስ" ጉዳይ ላይ ተነጋገሩ።
Published 11/11/24
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ኅብረት የድጋፍ እና ማረጋጋት የሶማሊያ ተልዕኮ (AUSSOM) መታገዷን የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስትር ተናገሩ። በደቡብ ሱዳን ጎርፍ 379,000 ሰዎች አፈናቀለ። በናይጄሪያ ላኩራዋስ የተባለ አዲስ የሽምቅ ተዋጊ በፈጸመው ጥቃት 15 ሰዎች ተገደሉ። በፓኪስታን የባቡር ጣቢያ በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ 24 ሰዎች ተገደሉ። እስራኤል እና ሐማስ ወደ ድርድር ለመመለስ ከልብ ፈቃደኝነታቸውን እስኪያሳዩ ድረስ ቃጣር በጋዛ ተኩስ እንዲቆም የምታደርገውን ጥረት ልታቆም ነው። ኢራን ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ለአራት ዓመታት ሥልጣን ላይ ሣሉ ያሳደሩባትን ከፍተኛ ጫና በሁለተኛ የሥልጣን ዘመናቸው እንዲተዉት ጥሪ አቀረበች።
Published 11/09/24
አርስተ ዜና፤ --በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን አቸፈር ወረዳ ባለፈው ማክሰኞ ጥቅምት 26/2017 በድሮን በተፈፀመ ጥቃት ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸውንና 9 መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ። --የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስቴር በፍራንኮ ቫሉታ ሸቀጦችን ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባት ከዛሬ ጀምሮ አገደ። --አቶ ዮሃንስ ቧያሌው 1ኛ ተከሳሽ በሆኑበት መዝገብ የተከሰሱና ጉዳያቸው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እየታየ ያለው ግለሰቦች ለሕዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም ተቀጠሩ። --በጋዛ ጦርነት ከተገደሉት ውስጥ 70 በመቶ ያህሉ ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸው መለየቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። ሙሉዉን ዜና ያድምጡ!
Published 11/08/24
ኦሮሚያ ክልል ውስጥ የወረዳ ባለሥልጣናትን ጨምሮ 48 ሰዎች የተገደሉበትን ጥቃት እየመረመረ መሆኑን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ አስታወቀ። የባሕርዳር ከተማ አስተዳደር በእገታና በዘረፋ ተሰማርተው ነበር ያላቸውን ክ129 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጠ። የጀርመን የፋይናንስ ሚኒስትር ከሥልጣናቸው መነሳታቸውን ተከትሎ የሀገሪቱ ጥምር መንግሥት ቀውስ ውስጥ ገብቷል። ተቃዋሚዎች አስቸኳይ ምርጫ እንዲካሄድ ግፊት እያደረጉ ነው። ፕሬዝደንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር የጥምር መንግሥቱ ለገባበት ቀውስ መፍትሄ ለማምጣት ኃላፊነት የተሞላበት አካሄድ እንዲኖር ፖለቲከኞቹን አሳስበዋል።
Published 11/07/24
DW Amharic አርስተ ዜና በአማራ ክልል እየተባባሰ የሄደው ግጭት እንዳሳሰባት አሜሪካ አስታወቀች። በኢትዮጵያ ግጭቶች እልባት ያገኙ ዘንድ የፖለቲካ ውይይቶች መደረግ አለባቸው፤ የሚል አቋም እንዳላትም ገልፃለች።--አሜሪካ 47 ኛዉን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን እያካሄደች ነዉ። ሁለቱ ፕሬዚዳንታዊ እጩዎች በየፊናቸዉ እንደሚያሸንፉ ተናግረዋል። በሌላ በኩል የአሜሪካ የደኅንነት ባለስልጣናት «የውጭ ኃይሎች» ያሏቸዉ የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እምነት እንዲያጣ ሙከራ እያደረጉ ነው ሲሉ እየከሰሱ ነዉ።--የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሜር ዜሌንስኪ 11,000 የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ሩስያ ድንበር ኩርስክ ግዛት መግባታቸዉን በስጋት ገለፁ።
Published 11/05/24
በሶማሊያ ዋና ከተማ መቅዲሹ ላይ አሸባብ ባደረሰው ጥቃት የተመድ ሠራተኞችን ጨምሮ በርካቶች መገደላቸው ተነገረ። ጥቃቱ የደረሰው ከመቃዲሹ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የሚገኝ ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግለት ስፍራ ነው። ስፔን ውስጥ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ዛሬም የጎርፍ ሰለባዎችን መፈለግ ቀጥለዋል። ቫለንሲያ ግዛት በጎርፍ ከደረሰባት አደጋ ጋር እየታገለች ዛሬ ኃይለኛ ዝናብ የወረደባት ባርሴሎና ከተማ በተጠንቀቅ ላይ ትገኛለች። የሱዳን ጦር አዛዥ አብደልፈታህ አል ቡርሀን የባለሥልጣናት ሹም ሽር አደረጉ። አራት አዳዲስ ሚኒስትሮችንም ሰየሙ። የእስራኤል ጦር ሰሜን ጋዛ ውስጥ የሚገኘው የክትባት ማዕከል ላይ ጥቃት አላዳረስኩም አለ።
Published 11/04/24