Description
ማሊ ውስጥ የቆየው የተመድ ተልዕኮ በዛሬው ዕለት ለሀገሪቱ ወታደራዊ ኹንታ ባለሥልጣናት ወታደራዊ ሰፈሩን አስረከበ። በያዝነው ዓመት ታኅሣስ ማለቂያ አካባቢ ተልዕኮው አጠቃሎ ከማሊ ይወጣል።
ዓመታዊው የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ተከታታይ ጉባኤ የተነሳለትን አላማ ማሳካት ተስኖታል የሚሉ ወገኖች የማሳሰቢያ ደብዳቤ ለጉባኤው አቀረቡ።
ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የመካከለኛው ምሥራቅ እና የሩሲያ እና የዩክሬን ጦርነት መቆም አለበት አሉ።
የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ ከሁለት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ከሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ተነጋገሩ።