የዓለም ዜና፤ ኅዳር 09 ቀን 2017 ዓ.ም
Listen now
Description
DW Amharic አርስተ ዜና፤ --የቡድን 20 አገሮች የሁለት ቀናት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ብራዚል ሬዮዴጄኔሮ ላይ ጀመረ። 19 በእንዱስትሪ የበለጽጉ እና ያደጉ የዓለም አገሮች እንዲሁም የአውሮጳ ህብረትን ያካተተዉ የቡድን 20 ጉባዔን ለመሳተፍ ሀገራት መሪዎች ከፍተኛ ልዑካኖቻቸዉን አስከትለዉ በጉባኤዉ ለመሳተፍ ሬዮዴጄኔሮ ገብተዋል። --የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደዓ ዛሬ በቀጠሮያቸው መሰረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀረቡ። --የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይላት በጦርነቱ ለተፈፀመዉ ሰብዓዊ ጥሰት ኃላፊነት እንደማይወስዱ ገለፁ።
More Episodes
-የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2017 ዓመት 582 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አጠደቀ።የምክር ቤት አባላት ተጨማሪዉ በጀት የዋጋ ግሽበትን ያጠናክራል፣ ግብር ከፋዩን ያማርራል፤ ምጣኔ ሐብቱን ያዉካል የሚል ተቃዉሞ አንስተዉ ነበር ግን በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።-የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ 3 የመብት ተሟጋች ድርጅቶችን ማገዱን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ተቃወመዉ፤ አምንስቲ ኢንተርናሽናል አወገዘዉ።-እስራኤልና የሊባኖሱ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሒዝቡላሕ...
Published 11/26/24
Published 11/26/24
አርስተ ዜና --«G7» ሰባቱ በኢንዱስትሪ የበለፀጉት አገራት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በመካከለኛዉ ምስራቅና በሩስያ ዩክሬይን ቀዉስ ጉዳይ ላይ ለመምከር የሁለት ቀን ስብሰባ ጣልያን ዉስጥ ጀመሩ። ሚኒስትሮቹ በእስራኤል ባለስልጣናትና በሃማዝ ወታደራዊ አዛዥ ላይ የተላለፈዉ የእስር ማዘዣም የመወያያ ርዕሳቸዉ ነዉ።--“ፅንፈኛና ሽብርተኛ” ያላቸው አካላት ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ፈጸሙት ያለውን ግድያ፤ የአማራ ከልል መንግሥት አወገዘ፡፡ ያም ሆኖ፤...
Published 11/25/24