Episodes
የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በኦሮሚያ ክልል በተፈጸሙ ጥቃቶች 120 የመንግሥት ወታደሮች ገድያለሁ አለ። ህወሓት በፕሪቶሪያ ግጭት የማቆም ሥምምነት የገባቸውን ግዴታዎች እየፈጸመ አይደለም ሲል የኢትዮጵያ መንግሥትን ከሰሰ። አሜሪካ “ታሪካዊ“ ያለችው “የርስ በርስ ጦርነት ያቆመ ሥምምነት“ የተፈረመበትን ሁለተኛ ዓመት በማስመልከት በኢትዮጵያ ግጭት እንዲቆም ጥሪ አቅርባለች። የወባ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ዋንኛ የሕብረተሰብ ጤና ተግዳሮት እንደሆነ የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ። ከታኅሳስ 22 ቀን 2016 እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ብቻ 7.3 ሚሊዮን የወባ ሕሙማን መመዝገባቸውን፤ 1157 ሰዎች መሞታቸውን አስታውቋል።
Published 11/02/24
*በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ በታጠቁ ኃይሎች በደረሰ ጥቃት ቢያንስ የ40 ንጹሃን ሰዎች ህይወት አለፈ።
*በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ዛሬ ጠዋት በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ10 ሰዎች ሕይወት አለፈ ፡፡
*ሁለቱ የህወሓት ቡድኖች በልዩነታቸው ላይ ለመነጋገር እንደተስማሙ ተነገረ።
*የጀርመን ፌደራል መንግስት በሀገሩ የሚገኙ የኢራን ቆንስላዎች በሙሉ እንዲዘጉ ወሰነ።
* እስራኤል ሊባቦስ እና ጋዛ ውስጥ ጥቃት ሰነዘረች
Published 11/01/24
DW Amharic -በአማራ ክልል ያለውን ቀውስ ለመፍታት የሰላም ጥረት አለመሳካቱን ጠቅላይ ሚንስትሩ መግለፃቸው-ከአየር ንብረት እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ጋር ተዳምሮ የግጭት መስፋፋት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለከፋ ችግር ዳርጓል መባሉ-ሶማሊያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አዲስ የሽግግር ተልዕኮ ለማቋቋም መወሰኑን ማወደሷ-እስራኤል ሊባኖስ ውስጥ በፈፀመችው የአየር ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ መባሉ-ሰሜን ኮሪያ አህጉር አቋራጭ የባሊስቲክ ሚሳኤል መተኮሷን መግለጿ በዛሬው የዓለም ዜና የተካተቱ ርዕሶች ናቸው።
Published 10/31/24
በዎላይታ ዞን እና በሲዳማ ክልል ውስጥ ትናንት በደረሰ መሬት መንሸራተት የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አለፈ። የአደጋው መንስኤ በሌሊት የጣለው ከባድ ዝናብ እንደሆነ ተገልጿል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን በፀጥታ አባላት የጅምላ እሥር እየተፈጸመ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች አመለከቱ። መንስኤው ከሸኔ አለያም ከፋኖ ጋር ግንኙነት አላችሁ የሚል ነው ተብሏል።
የሴኔጋል ባሕር ኃይል ባለፉት 10 ቀናት 600 የሚሆኑ ሕገወጥ ስደተኞችን ከባሕር ላይ መያዙን አስታወቀ።
ኢራን በእስራኤል ጥቃት የሚሳኤል ማምረቻዎቼ አልተጎዱም አለች።
Published 10/30/24
አ.አ፥ በተወካዮች ምክር ቤት አባል የፍትሕ ሚንስትር ላይ ትችት ቀረበ፤ መቐለ፥ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የመቐለ ከንቲባን ከሥልጣን ማገዱን ዐሳወቀ፤ ካርቱም፥ ከሱዳን አንድ ሦስተኛ ግድም ነዋሪ ስደተኛ አለያም ተፈናቃይ ነው፤ ኒውዮርክ፥ በእሥራኤል የUNRWA መታገድ በፍልስጥኤም ስደተኞች ላይ የከፋ መዘዝ ያስከትታል ሲል ተመድ አስጠነቀቀ፤
Published 10/29/24
DW Amharic--ግብፅ አራት የሃማስ ታጋች እስራኤላውያንን በተወሰኑ ፍልስጤማዉያን እስረኞች ለመለወጥ በጋዛ የሁለት ቀን የተኩስ አቁም እንዲደረግ ሀሳብ አቀረበች። የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ ኧልሲሲ ይህን ያሉት ከአንድ ዓመት በላይ የዘለቀውን የጋዛ ጦርነት ለማስቆም የሚደረገው ድርድር ድጋሚ በተጀመረበት ወቅት ነው፡፡
--125 ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ ወደ ሃገራቸዉ መመለሳቸዉን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
--የዩናይትድ ስቴትስ የሪፓብሊካን እጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ተቀናቃኛቸዉ የዲሞክራቶች እጩ ተወዳዳሪ ካማላ ሃሪስ ዩናይትድ ስቴትስን እያወደሙ ነዉ ሲሉ ከሰሱ ። ዝርዝሩን ያድምጡ!
Published 10/28/24
ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ነገ ሰኞ አጀንዳ ማሰባሰብ ሊጀምር ነው። የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ኻሚኒ እስራኤል በሀገራቸው ላይ ባለፈው አርብ የፈጸመችው ጥቃት ሊናናቅም ሆነ ሊጋነን እንደማይገባ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በበኩላቸው ጥቃቱ የታለመለትን ዓላማ አሳክቷል ብለዋል። በጋዛ እስራኤል በፈጸመቻቸው ጥቃቶች 45 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የፍልስጤም ባለሥልጣናት አስታወቁ። ዮሚፍ ቀጀልቻ በቫሌንሺያ፤ ሐዊ ፈይሳ በፍራንክፉርት ክብረ ወሰን በማሻሻል የግማሽ ማራቶን እና የማራቶን ውድድሮች አሸነፉ። የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ አሥራት ኃይሌ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ።
Published 10/27/24
-የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን የመነጋገሪያ ርዕሥ ለመሰብሰብ ጂጂጋ-ሶማሌ ክልል የጠራዉ ጉባኤ የተሳታፊዎች ማንነት ዉዝግብ ማስከተሉ ተነገረ።ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያም ዉዝግብ መነሳቱን አረጋግጠዋል።-የእስራኤል ጦር ደቡባዊ ሊባኖስ ዉስጥ የሠፈረዉን የተባበሩት መንግሥታት ሠላም አስከባሪ ሠራዊት በድጋሚ ማዝቃቱን ሠራዊቱ አስታወቀ።-የሩሲያና የምዕራባዉያን መንግስታት ዉዝግብ ወደ ኮሪያ ልሳነ ምድርም እየተዛመተ ነዉ።ሩሲያ ከሰሜን ኮሪያ ጋር በጦር ኃይል የመደጋጋገፍ ዉል መፈራረሟ ከዋሽግተን እስከ ሶል የሚገኙ የተባባሪ ሐገራት መንግሥታትን አስግቷል።የዜናዉ መልዕክት የእስካሁኑ ነበር
Published 10/25/24
ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና የዜና ትንታኔዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ።
የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በዩቲዩብ፣ በአፕል ፖድካስት፣ በስፖቲፋይ እና በየትኛውም የፖድካስት ምርጫዎን በምታገኙባቸው መንገዶች ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።
Published 10/24/24
አስገድዶ መሰወር፣ እገታ እና እየደረሰ ያለው ቀውስ
የእስራኤል ድሮኖች በታሪካዊት ከተማ ያካሄዱት ድብደባ
ሩስያና ኒኩለር ጦር መሳሪያ የመጠቀም ስጋት
የብሪክስ መድረክ የአዳጊ አገራት ድምጽና ፍላጎት ማንጸባረቂያ እንዲሆን ተጠየቀ
Published 10/23/24
የነአቶ ዮሃንስ ቧያሌው የፍርድቤት ውሎ
እስራኤል የሒዝቦላህ የፋይናንስ ተቋማትን በአየር ማውደሟን
የእስራኤል የመከላከያ ሰራዊት ሊባኖስን ይቅርታ ጠየቀ።
አሜሪካ ለዩክሬይን የ400 ሚልዮን ዶላር ወታደራዊ ድጋፍ እንደምትሰጥ ይፋ አደረገች።
Published 10/23/24
ትናንት ማምሻውን በአዲስ አበባ መርካቶ የተነሳውና ለረዥም ሰዓት የቆየው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ሳያደርስ እንዳልቀረ እየተነገረ ነው። እሳቱ እስከ ዛሬ ማለዳ ድረስ ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ሥር አልዋለም ነበር። መስኤውም እልታወቀም።
ከአንድ ወር በላይ ተዘግቶ የቆየው የኢትዮ ሱዳን ደንበር ከትናንት አንስቶ ጀምሮ እንደገና ተከፍቶ አገልግሎት መጀመሩን የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር አስታወቀ።
የሱዳን ጦር ባካሄደው የአየር ጥቃት ቢያንስ 31 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው የመብት ተሟጋቾች አስታወቁ።
የአውሮጳ ዓርላማ ከታገደው የሩሲያ ንብረት ላይ ለዩክሬን 35 ቢሊየን ዩሮ ብድር አጸደቀ።
Published 10/22/24
በጫሞ ሐይቅ ላይ በደረሰው የጀልባ መስጠም አደጋ እስከአሁን 12 አስከሬን መገኘቱን
እስራኤል 3 የሒዝቦላህ ከፍተኛ አመራሮች ገደልኩ አለች
በጋዛ እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት 87 ፍልስጤማውያን ተገደሉ
ሾልኮ የወጣው ሚስጢራዊ ሰነድ
Published 10/21/24
-የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ከፍተኛ ባለሥልጣን፣ የሠላም ሚንስትር ደኤታና የኦሮሚያ ምክር ቤት እንደራሴ ታዬ ደንደዓ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ታጥቃዋል በሚል መከሰሳቸዉን ዉድቅ አደረጉት።ከአምና ታሕሳስ ጀምሮ ከሥልጣን ተነስተዉ የታሰሩት አቶ ታዬ ጦር መሳሪ መታጠቃቸዉን አልካዱም።መከሰሳቸዉን ግን አልተቀበሉትም።-----የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክን ከፍተኛ ኒሻን ዛሬ ተሸለሙ።-የእስራኤል ጦር የሐማስን መሪ ያሕያ ሲንዋርን መግደሉን የፍልስጤሙ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አመነ።
Published 10/18/24
በአማራ ክልል የሚዋጉት የኢትዮጵያ መንግሥት ጦርና የፋኖ ታጣቂዎች ለሰላማዊ ሰዎችና ተቋማት ጥበቃና ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የክልሉ ዩኒቨርስቲዎች መድረክ ወይም ፎረም ጠየቀ።----የኬንያ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) የሐገሪቱ ምክትል ፕሬዝደንት ሪጋዚ ጋሻጉዋ ሥልጣን መልቀቅ አለባቸዉ-የለባቸዉም በሚለዉ ሐሳብ ላይ መከራከር ጀመረ።ምክትል ፕሬዝደንቱ የተያዘባቸዉን የወንጀል ጭብጥ በሙሉ ፖለቲካዊ በማለት ክደዋል።-የኢራንና የእስራኤል ባለሥልጣናት አሁንም እየተዛዛቱ ነዉ።ሊባኖስና ጋዛ ዛሬም ይወድማሉ።ዩናይትድ ስቴትስና ጀርመን ለእስራኤል ጦር መሳሪያ ማስታጠቃቸዉን ቀጥለዋል።
Published 10/16/24
የሶማሊያና የግብጽ ፕሬዝደንቶች በኤርትራ ይፋዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው። የሁለት ሃገራት መሪዎች ከኤርትራው ፕሬዝደንት ጋር በሁለትዮሽ፤ በአፍሪቃ ቀንድና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ተገልጿል።
የተመድ በመላው ዓለም ወጣቶች ለዘርፈ ብዙ ጥቃቶች መጋለጣቸውን አመለከተ። የተመድ ታይቶ ለማይታወቅ የጥቃት ማዕበል እና ጦርነት ባመጣው ጾታዊ ጥቃት እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ፤ ረሃብና መፈናቀል ተጋልጠዋል።
ግብጽ በሱዳን ጦርነት በአየር ድብደባ ተሳትፋለች በሚል ከፈጥኖ ደራሹ ኃይል መሪ የቀረበባትን ክስ አስተባበለች።
የጎርጎሪዮሳዊው ዓመት 2024 የስነጽሑፍ የኖቤል ሽልማት ለደቡብ ኮርያዋ ደራሲ ሃን ካን ተሰጠ።
Published 10/10/24