የጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
Listen now
Description
በዎላይታ ዞን እና በሲዳማ ክልል ውስጥ ትናንት በደረሰ መሬት መንሸራተት የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አለፈ። የአደጋው መንስኤ በሌሊት የጣለው ከባድ ዝናብ እንደሆነ ተገልጿል። በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን በፀጥታ አባላት የጅምላ እሥር እየተፈጸመ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች አመለከቱ። መንስኤው ከሸኔ አለያም ከፋኖ ጋር ግንኙነት አላችሁ የሚል ነው ተብሏል። የሴኔጋል ባሕር ኃይል ባለፉት 10 ቀናት 600 የሚሆኑ ሕገወጥ ስደተኞችን ከባሕር ላይ መያዙን አስታወቀ። ኢራን በእስራኤል ጥቃት የሚሳኤል ማምረቻዎቼ አልተጎዱም አለች።
More Episodes
-የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2017 ዓመት 582 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አጠደቀ።የምክር ቤት አባላት ተጨማሪዉ በጀት የዋጋ ግሽበትን ያጠናክራል፣ ግብር ከፋዩን ያማርራል፤ ምጣኔ ሐብቱን ያዉካል የሚል ተቃዉሞ አንስተዉ ነበር ግን በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።-የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ 3 የመብት ተሟጋች ድርጅቶችን ማገዱን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ተቃወመዉ፤ አምንስቲ ኢንተርናሽናል አወገዘዉ።-እስራኤልና የሊባኖሱ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሒዝቡላሕ...
Published 11/26/24
Published 11/26/24
አርስተ ዜና --«G7» ሰባቱ በኢንዱስትሪ የበለፀጉት አገራት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በመካከለኛዉ ምስራቅና በሩስያ ዩክሬይን ቀዉስ ጉዳይ ላይ ለመምከር የሁለት ቀን ስብሰባ ጣልያን ዉስጥ ጀመሩ። ሚኒስትሮቹ በእስራኤል ባለስልጣናትና በሃማዝ ወታደራዊ አዛዥ ላይ የተላለፈዉ የእስር ማዘዣም የመወያያ ርዕሳቸዉ ነዉ።--“ፅንፈኛና ሽብርተኛ” ያላቸው አካላት ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ፈጸሙት ያለውን ግድያ፤ የአማራ ከልል መንግሥት አወገዘ፡፡ ያም ሆኖ፤...
Published 11/25/24