የጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
Listen now
Description
ትናንት ማምሻውን በአዲስ አበባ መርካቶ የተነሳውና ለረዥም ሰዓት የቆየው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ሳያደርስ እንዳልቀረ እየተነገረ ነው። እሳቱ እስከ ዛሬ ማለዳ ድረስ ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ሥር አልዋለም ነበር። መስኤውም እልታወቀም። ከአንድ ወር በላይ ተዘግቶ የቆየው የኢትዮ ሱዳን ደንበር ከትናንት አንስቶ ጀምሮ እንደገና ተከፍቶ አገልግሎት መጀመሩን የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር አስታወቀ። የሱዳን ጦር ባካሄደው የአየር ጥቃት ቢያንስ 31 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው የመብት ተሟጋቾች አስታወቁ። የአውሮጳ ዓርላማ ከታገደው የሩሲያ ንብረት ላይ ለዩክሬን 35 ቢሊየን ዩሮ ብድር አጸደቀ።
More Episodes
-የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2017 ዓመት 582 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አጠደቀ።የምክር ቤት አባላት ተጨማሪዉ በጀት የዋጋ ግሽበትን ያጠናክራል፣ ግብር ከፋዩን ያማርራል፤ ምጣኔ ሐብቱን ያዉካል የሚል ተቃዉሞ አንስተዉ ነበር ግን በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።-የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ 3 የመብት ተሟጋች ድርጅቶችን ማገዱን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ተቃወመዉ፤ አምንስቲ ኢንተርናሽናል አወገዘዉ።-እስራኤልና የሊባኖሱ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሒዝቡላሕ...
Published 11/26/24
Published 11/26/24
አርስተ ዜና --«G7» ሰባቱ በኢንዱስትሪ የበለፀጉት አገራት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በመካከለኛዉ ምስራቅና በሩስያ ዩክሬይን ቀዉስ ጉዳይ ላይ ለመምከር የሁለት ቀን ስብሰባ ጣልያን ዉስጥ ጀመሩ። ሚኒስትሮቹ በእስራኤል ባለስልጣናትና በሃማዝ ወታደራዊ አዛዥ ላይ የተላለፈዉ የእስር ማዘዣም የመወያያ ርዕሳቸዉ ነዉ።--“ፅንፈኛና ሽብርተኛ” ያላቸው አካላት ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ፈጸሙት ያለውን ግድያ፤ የአማራ ከልል መንግሥት አወገዘ፡፡ ያም ሆኖ፤...
Published 11/25/24