የዓለም ዜና፤ ጥቅምት 18 ቀን 2017 ሰኞ
Listen now
Description
DW Amharic--ግብፅ አራት የሃማስ ታጋች እስራኤላውያንን በተወሰኑ ፍልስጤማዉያን እስረኞች ለመለወጥ በጋዛ የሁለት ቀን የተኩስ አቁም እንዲደረግ ሀሳብ አቀረበች። የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ ኧልሲሲ ይህን ያሉት ከአንድ ዓመት በላይ የዘለቀውን የጋዛ ጦርነት ለማስቆም የሚደረገው ድርድር ድጋሚ በተጀመረበት ወቅት ነው፡፡ --125 ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ ወደ ሃገራቸዉ መመለሳቸዉን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። --የዩናይትድ ስቴትስ የሪፓብሊካን እጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ተቀናቃኛቸዉ የዲሞክራቶች እጩ ተወዳዳሪ ካማላ ሃሪስ ዩናይትድ ስቴትስን እያወደሙ ነዉ ሲሉ ከሰሱ ። ዝርዝሩን ያድምጡ!
More Episodes
-የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2017 ዓመት 582 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አጠደቀ።የምክር ቤት አባላት ተጨማሪዉ በጀት የዋጋ ግሽበትን ያጠናክራል፣ ግብር ከፋዩን ያማርራል፤ ምጣኔ ሐብቱን ያዉካል የሚል ተቃዉሞ አንስተዉ ነበር ግን በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል።-የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ 3 የመብት ተሟጋች ድርጅቶችን ማገዱን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ተቃወመዉ፤ አምንስቲ ኢንተርናሽናል አወገዘዉ።-እስራኤልና የሊባኖሱ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሒዝቡላሕ...
Published 11/26/24
Published 11/26/24
አርስተ ዜና --«G7» ሰባቱ በኢንዱስትሪ የበለፀጉት አገራት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በመካከለኛዉ ምስራቅና በሩስያ ዩክሬይን ቀዉስ ጉዳይ ላይ ለመምከር የሁለት ቀን ስብሰባ ጣልያን ዉስጥ ጀመሩ። ሚኒስትሮቹ በእስራኤል ባለስልጣናትና በሃማዝ ወታደራዊ አዛዥ ላይ የተላለፈዉ የእስር ማዘዣም የመወያያ ርዕሳቸዉ ነዉ።--“ፅንፈኛና ሽብርተኛ” ያላቸው አካላት ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ፈጸሙት ያለውን ግድያ፤ የአማራ ከልል መንግሥት አወገዘ፡፡ ያም ሆኖ፤...
Published 11/25/24