አበራ ለማ፤ ከመምህርነት ወደ ጋዜጠኛነትና ደራሲነት
Listen now
Description
ከኢትዮጵያ አንጋፋና ስመ ገነን ጋዜጠኞችና ደራሲዎች ውስጥ ቀዳሚ ተጠቃሽ ከሆኑቱ ውስጥ አበራ ለማ አንዱ ነው። በማስታወቂያ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ራዲዮና አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ በግሉ ፕሬስ በአዕምሮ ጋዜጣ የጋዜጠኛነት ድርሻውን አበርክቷል። በድርሰት በረከቶቹም ሰሞነኛውን "የዓለማችን ምስጢራት" መፅሐፉን አክሎ ከ20 በላይ መፅሐፍትን ለተደራሲያን እነሆኝ ብሏል።
More Episodes
ሲስተር ሰላም ተገኝ፤ በፐርዝ - ምዕራብ አውስትራሊያ የአፍሪካውያን ማኅበረሰብ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚደንት፣ ወ/ሮ ውዳድ ሳሊም፤ በሜልበርን - ቪክቶሪያ የሕዝብ ጤና ደህንነት አንቂና ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ፤ በብሪስበን - ኩዊንስላንድ የደቡብ ማኅበረሰብ ማዕከል ማኔጂንግ ዳይሬክተር፤ የቤት ውስጥ ጥቃት / አመፅን ከኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ማኅበረሰባት አኳያ አሰናስለው ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።
Published 06/15/24
በፍሬድ ማየር ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ባለሙያዋ ዶ/ር ዕፀገነት አሰፋ፤ ባለፉት ሁለት ክፍለ ዝግጅቶቻችን ከመሀል ሜዳ እስከ ሀገረ አሜሪካ ያለፉበትን የሕይወት ጉዞ አንስተው አውግተዋል። በውይይታችን መቋጫ ከፋርማሲ ሙያቸው ጎን በሲያትል ከተማ ተሰማርተው ስላሉበት የቤት ግዢና ሽያጭ (Real Estate) የንግድ መስክ ይናገራሉ።
Published 06/14/24