“ በጥቃቅን እና አነስተኛ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሰዎች የተሻለ ብድርን ለማግኘት ቀረጥን በአግባቡ መክፈል ይኖርባቸዋል። “ - አቶ እስቅያስ መንግስቴ
Listen now
Description
አቶ እስቅያስ መንግስቴ የፋይናንስ የብድር ማስፈቀድ እና ማመቻቸት ስራ ባለሙያ ፤ በአውስትራሊያ በኤን ዜድ ባንክ ለ 14 አመታት ያገለገሉ ሲሆን በአሁን ሰአት ከሌሎች መሰል ባለሙያዎች ጋር በመሆን በግል የብድር ማስፈቀድ እና ማመቻቸት ስራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ። በተለይ ደግሞ ወደ ግሉ ተቋም የዞሩብት ምክንያት ለሚኖሩትበት የማህበረሰብ አባላት ብድርን በማስገኘት እና በማማከር ረገድ በበለጠ ለማገልገል ነው ይላል።
More Episodes
በፍሬድ ማየር ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ባለሙያዋ ዶ/ር ዕፀገነት አሰፋ፤ ባለፉት ሁለት ክፍለ ዝግጅቶቻችን ከመሀል ሜዳ እስከ ሀገረ አሜሪካ ያለፉበትን የሕይወት ጉዞ አንስተው አውግተዋል። በውይይታችን መቋጫ ከፋርማሲ ሙያቸው ጎን በሲያትል ከተማ ተሰማርተው ስላሉበት የቤት ግዢና ሽያጭ (Real Estate) የንግድ መስክ ይናገራሉ።
Published 06/14/24
በፍሬድ ማየር - ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የፋርማሲ ባለሙያ ዶ/ር ዕፀገነት አሰፋ፤ እንደምን ወደ ፋርማሲ ሙያ እንደዘለቁና በሙያው መስክ እንደተሠማሩ ያወጋሉ። የኢትዮጵያንና የአሜሪካ ፋርማሲዎች አሠራርን ነቅሰው ያስረዳሉ።
Published 06/13/24