Episodes
የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ማሻሻያ ባለሥልጣናቱ እንዳሉት ምን ያክል አገር በቀል ነው? መዋቅራዊ ችግር አለበት ለሚባለው ኤኮኖሚስ ምን ዓይነት መፍትሔ ይዞ ይመጣል? በገበያ ፍላጎት የሚመራ ተለዋዋጭ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት ተግባራዊ ሲሆን ሊመጣ የሚችለውን የብር የመግዛት አቅም መዳከም እና የዋጋ መናር ኢትዮጵያ እንዴት ትቋቋማለች?
Published 12/22/19
ሰሞኑን ይፋ የሆነው የአቶ ለማ ከኢህአዴግ ውህደት እና ከመደመር ፍልስፍና የመለየታቸው ዜና ማነጋገሩ ማስገረሙ ቀጥሏል። ክስተቱ ለህዝብ ጥያቄ ቆመናል የሚሉ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች አንድ ሆንን ብለው ሳያበቁ፣ የመለያያታቸው ዜና የመከተሉ ልምድ ሌላው ማሳያ ተደርጎ ሊወስድ እንደሚችል ተገምቷል።
Published 12/08/19
የሲዳማ ክልል የመሆን ጥያቄ በዞኑ በሚኖሩ ነዋሪዎች ከፍተኛ ድጋፍ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያወጣው የመጀመሪያ ደረጃ የህዝበ ውሳኔ ውጤት አሳይቷል። ሲዳማ 10ኛው የኢትዮጵያ ክልል ለመሆን በዋዜማ ላይ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ዞኑ ወደ ክልልነት ከመሸጋገሩ ጋር የተያያዙ፣ መልስ የሚሹ ጥያቄዎች አሁንም ይነሳሉ።
Published 12/01/19
«ወጣቱን መዉቀስ ብቻ ሳይሆን፤ ቆም ብለን ለወጣቱ ምን ያስፈልገዋል ብለን ልናስብ ይገባል። ለምን ወጣቱን ቀረብ ብለን አናወያይም? ለአዛዉንቶች የሚዲያ መድረክ ከምንሰጥ እና ግጭትን ከምናሰፋ ወጣቱን ቀረብ ብለን እናወያይ። ድሕነትና መሐይምነት ሲጋቡ አሁን እኛ ሃገር የሚታየዉን ችግር ወልደዋል። »
Published 11/17/19
«ወጣቱን መዉቀስ ብቻ ሳይሆን፤ ቆም ብለን ለወጣቱ ምን ያስፈልገዋል ብለን ልናስብ ይገባል። ለምን ወጣቱን ቀረብ ብለን አናወያይም? ለአዛዉንቶች የሚዲያ መድረክ ከምንሰጥ እና ግጭትን ከምናሰፋ ወጣቱን ቀረብ ብለን እናወያይ። ድሕነትና መሐይምነት ሲጋቡ አሁን እኛ ሃገር የሚታየዉን ችግር ወልደዋል። »
Published 11/17/19
የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ ኢህአዴግን ተችቷል። ይህንን ተከትሎ የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት በህወሓት መግለጫ የተነሱ ነጥቦችን የሚያጣጥል ምላሽ ሰጥቷል። የግንባሩ ሊቀመንበር አብይ አህመድም በስም ባይጠቅሱም ህወሓት ላይ ያነጣጠረ ትችት ሲሰነዝሩ ተደምጠዋል። የመቃቃሮቹ መንስኤዎች ምንድናቸው?
Published 10/27/19
በቅርቡ ይመሰረታል የተባለዉ ፓርቲ የብልጽግና ፓርቲ እንደሚባል ጋዜጠኞች በስፋት ሲያስነብቡት ተስተዉሎአል። በተለያዩ  ዘገባዎችም ኢህአዴግ አለቀለት፤ ዉህድ ፓርቲዉ እዉን የሚሆን ከሆነም የሃገሪቱ የፖለቲካ ሁኔታ ይቀየራል፤ ኢህአዴግ ከተቀየረም ጥሩ ይሆናል እያሉ ትንታኔ ሰጥተዋል። የኢህአዴግ ቀጣይ አቅጣጫ ወዴት?
Published 10/06/19
የኢትዮጵያ የትምህርት እና ስልጠና ሂደት በሚቀጥሉት 15 ዓመታት እንዴት መመራት እንዳለበት አቅጣጫ እና ምክረ ሀሳብ ያስቀመጠ “የትምህርት እና ስልጠና ፍኖተ- ካርታ” ተግባራዊ እንደሚደረግ በቅርቡ ተገልጿል።በፍኖተ ካርታው ላይ የተመሰረቱ፣ በትምህርት መዋቅሩ ላይ የሚደረጉ ለውጦች ለህዝብ ይፋ ከተደረጉ በኋላ ጉዳዩ መወያያ ሆኖ ሰንብቷል።
Published 09/01/19