መዝናኛ፦ ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ በአዲስ የመድረክ ስራ
Listen now
Description
ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ ትናንት ነሐሴ 25 ምሽት አዲስ የ“ስታንድ አፕ” ኮሜዲ ስራውን በአዲስ አበባው አዶት ሲኒማ እና ቴአትር አዳራሽ አቅርቧል። ወጣቱ ሳቅ ፈጣሪ በሳል ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ትችቶችን፤ በሀገሪቱ ውስጥ ይስተዋላሉ ካላቸው ግድፈቶች መነሻ እየነቀሰ፤ በሳቢ እና አስቂኝ አካላዊ እንቅስቃሴ እያዋዛ ስራዎቹን ለታዳሚዎቹ አቅርቧል።