Episodes
ከአዲስ አበባ በስተደቡብ አቅጣጫ በ275 ኪሜ ርቀት ላይ የሚኘው የወንዶገነት የመዝናኛ ስፍራ በ1949 ዓም በንጉስ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ልጅ ልዕልት ተናኘወርቅ እንደተቆረቆረ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የወንዶገነት የመዝናኛ ስፍራ ጥቅጥቅ ባሉ ደኖችና በሰንሰለታማ ተራሮች የተከበበ ነው።
Published 11/24/19
በአዲስ አበባ በሊስትሮ ስራ ከሚተዳደረው ወጣት አብረሃም ሲሳይ ጋር ጋዜጠኛ ዮሀንስ ገብረ እግዚያብሔር ቆይታ አድርጓል
Published 11/17/19
Published 09/29/19
ወደ ፈረንሳይ ፓሪስ ሰሞኑን ጎራ ብላ የነበረችው ዶክተር ምህረት አያሌው ማንደፍሮ ናት። የካን የፊልም ፌስቲቫል ላይ ከፓሪሷ ዘጋቢያችን ሐይማኖት ጥሩነህ ጋር ተገናኝተው ቆይታ አድርገዋል።
Published 09/08/19
ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ ትናንት ነሐሴ 25 ምሽት አዲስ የ“ስታንድ አፕ” ኮሜዲ ስራውን በአዲስ አበባው አዶት ሲኒማ እና ቴአትር አዳራሽ አቅርቧል። ወጣቱ ሳቅ ፈጣሪ በሳል ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ትችቶችን፤ በሀገሪቱ ውስጥ ይስተዋላሉ ካላቸው ግድፈቶች መነሻ እየነቀሰ፤ በሳቢ እና አስቂኝ አካላዊ እንቅስቃሴ እያዋዛ ስራዎቹን ለታዳሚዎቹ አቅርቧል።
Published 09/01/19
በተወሰኑ ወጣቶች ተነሳሽነት በ2004 ዓ.ም አገልግሎት መስጠት የጀመረችው ፊደል ሠራዊት ቤተ ንባብ በአባላቶችዋና ሌሎች በጎ አድራጊዎች የተበረከቱ መፅሕፍት ለሌሎች አንባብያ እንዲደርስ በማድረግ የንባብ ባሕል እንዲያድግ እንደምትሰራ አባላቶችዋ ይናገራሉ፡፡
Published 08/25/19
«በ 50 ዎቹ ዓመታት መጨረሻ ጋሽ ጥላሁንን፤ አለማየሁ እሸቴን እና ታምራት ሞላን የመሳሰሉ እንቁዎች ሰምቼ ከሙዚቃ ፍቅር ያዘኝ» ድምፃዊ የግጥምና ዜማ ደራሲ እንዲሁም የሙዚቃ አቀናባሪ አንጋፋዉ አርቲስት አያሌዉ መስፍን። ከሁሉ ከሁሉ የአዲስ አበቤ ፍቅረኛሞች ቀጠሮአቸዉ አያሌዉ መስፍን ሙዚቃ ቤት ጋር እንደነበር የሚያስታዉስ ያስታዉሰዋል።
Published 07/28/19
የሰመርጃም የሬጌ ፌስቲቫል ከዓርብ ዕለት አንስቶ እስከ ዛሬ እሁድ እኩለ ሌሊት ድረስ በቦን አቅራቢያ በምትገኘው የኮሎኝ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በየዓመቱ የሚካሄደው ይሔው ድግስ ላይ ከአለም ታዋቂ የሆኑ በተለይም የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኞች እና የሙዚቃው አፍቃሪያን ይሰበሰባሉ።
Published 07/07/19
አሁንም ሆነ በፊትም የሚጽፈው ለገንዘብ ሳይሆን የስነ ጽሁፍ ጥሙን ለማርካት መሆኑን የሚናገረው ዳዊት ከአሁን በኋላ የግጥም መፀሀፍ ለማሳተም አያስብም። ተጽፈው የተቀመጡ ሌሎች ድርሰቶቹን ግን በቅርቡ የማሳተም እቅድ አለው።
Published 06/30/19
በአዲስ አበባ የቴሌቢዥን ፖሊስ ፕሮግራም ብዙዎች ያስታውሱታል። አሁን ደግሞ በአርቲስ ቲቢ በአብይ ጉዳይ የቴሌቢዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ነው፤ ጋዜጠኛ መላኩ ብርሃኑ።
Published 06/16/19