Episodes
የግንቦት 18 ቀን 2011 ዓም ስርጭት
Published 05/26/19
ወጣቱ ሙዚቀኛ አቤል ሙሉጌታ እንነጋገር የሚለውን 3ኛ የሙዚቃ አልበሙን ለሙዚቃ አድማጭ ቤተሰብ አበርክቷል፡፡ ተፈጥሮን የመረዳትና የማክበር እንዲሁም የማድነቅ ጉዳዮችን የዳሰሰበት ይህ አልበሙ ግጥምና ዜማውም የተሰራው በራሱ በአቤል ነው፡፡ከDW ጋር ያደረገውን ቆይታ የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው መከታተል ይችላሉ።
Published 05/26/19
ከበደ አኒሳ ለኢትዮጵያ ሔራልድ፣ ቮይስ ኦፍ ኢትዮጵያ እንግሊዘኛ ጋዜጦች እንዲሁም ለዛሬይቱ ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ድምጽ የአማርኛ ጋዜጦች ለረጅም አመታት የሰሩ አንጋፋ ጋዜጠኛ ናቸው። ኢትዮጵያ ትቅደም የተባለውን መፈክር ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሙበት እሳቸው እንደነበሩ ያስታውሳሉ።
Published 05/19/19
በፊልም ሥራዎች ላይ መተወን የጀመረው በዘጠኝ ዓመቱ ነው። ላለፉት ሰባት ዓመታትም 23 ፊልሞችን ተውኗል። ያልታሰበው መጀመሪያ በትወና የተሳተፈበት ፊልም ነው፤ በዘጠኝ ዓመቱ። ብላቴና የሚለው ደግሞ ሁለተኛው። የ16 ዓመቱ ታዳጊ ወጣት እዮብ ዳዊት። ከአዳጊው ወጣት የፊልም ተዋናይ እዮብ ዳዊት ጋር የነበረንን ቆይታ ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ። 
Published 02/24/19
ከአስር አመታት በኋላ ሰባት አመታት የፈጀበትን አልበም ለአድናቂዎቹ ይዞ ቀርቧል ጎሳዬ ተስፋዬ። ሲያምሽ ያመኛል የሙዚቃ አልበሙ በአድናቂዎቹ ዘንድ እንደተወደደ ይነገራል። ከረጅም ዓመታት ቆይታ በኃላ ባወጣው የሙዚቃ አልበም ሁሉም ግጥምና ዜማ ለየት ያሉ ናቸው ይላል። ሙዚቃን ከጀመረበት አንስቶ የሙዚቃ ህይዎቱ ውጣ ውረድ እንደነበረው ይናገራል።
Published 02/10/19
ለኢትዮጵያውያን የትያትር አፍቃሪያን አለማየሁ ታደሰ የሚለው ስም እንግዳ አይደለም። ስመ ጥሩው ተዋናይ ከ32 በላይ የመድረክ ትያትሮች ላይ በተዋናይነት ተሳትፏል። በበርካታ ፊልሞች ላይ ችሎታውን ያስመሰከረው አለማየሁ ባለፈው ሳምንት ለስምንተኛ ጊዜ በተካሄደው የለዛ የሬድዮ ዝግጅት የሽልማት ስነ ስርዓት የዓመቱ ምርጥ ተብሎ ተሸልሟል። 
Published 10/28/18
ተዋናይ ቅድስት ስዩም በካን የፊልም ፌስቲቫል ላይ ከተመረጡ 15 ፊልሞች መካከል አንዱ በሆነውና በ 88ኛ የኦስካር ፊልም ውድድር ላይ በእጬነት ቀርቦ በነበረው LAMM ፊልም ላይ ተጫውታለች።በቅርቡ ደግሞ በሌላ ፎርቱና በተባለው ፊልም ላይ ተካፍላለች። የዛሬው የመዝናኛ ዝግጅት እንግዳችን ናት።
Published 10/14/18
በለንደን የሚገኘው የቪክቶሪያ እና አልበርት ሙዚየም ከ150 ዓመታት በፊት ከኢትዮጵያ ከተዘረፉ ቅርሶች መካከል የተወሰኑትን መርጦ ባለፈው ሚያዝያ ወር ለህዝብ ዕይታ ማብቃቱ ይታወሳል። ከመቅደላ በተዘረፉት ቅርሶች ውዝግብ ውስጥ የሰነበተው ሙዚየሙ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ የኢትዮጵያ የባህል ቀንን አዘጋጅቶ ነበር።
Published 10/07/18