Episodes
በኢትዮጵያ የኤሌክትሮኒክ ግብይት የተሰማሩ ጀማሪ ኩባንያዎች ብቅ ብቅ እያሉ ነው። ከእነዚህ አንዱ የሆነው አስቤዛ መተግበሪያውን ወይም ድረ-ገጹን በመጠቀም ከመደብሮች እንጀራና የባልትና ውጤቶችን ጨምሮ የተለያዩ ነገሮች ለሚገዙ ደንበኞች ካሉበት ያደርሳል። የኩባንያው መሥራች በረከት ታደሰ አስቤዛ እንደ አማዞን የራሱ መደብር እንዲኖረው ይመኛል
Published 05/05/21
Published 12/25/19
የቻይናው አሊባባ ግሩፕ የዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ የግብይት ማዕከልን በኢትዮጵያ ለመመስረት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር ህዳር 15 ተፈራርሟል። “ንግድና ዲጂታል ኢኮኖሚን የሚያበረታታ ነው” የተባለለት ማዕከሉ የላቀ ቴክኖሎጂ፣ መሰረተልማት፣ አገልግሎት አሰጣጥና የቁጥጥር ማዕቀፍ እንደሚኖረው ተገልጿል።
Published 11/27/19
Published 10/09/19
ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ​​​​​​​በሚቀጥሉት ስምንት አመታት 4 ቢሊዮን ሕዝብ የገመድ አልባ የተንቀሰቃሽ ስልክ ግንኙነት አምስተኛ ትውልድ (5G) ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ይሆናል። እስከ መጪው ጥር ወር መጨረሻ ድረስ ይኸው ቴክኖሎጂ በ25 አገራት ሥራ ይጀምራል። አሜሪካ፣ ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያና ጃፓን ቀዳሚ ናቸው። ከሰሐራ በታች ያሉ አገራት ይዘገያሉ
Published 09/25/19
የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የልዑካን ቡድን ባለፈው ሳምንት ወደ ጀርመን መዲና በርሊን በመምጣት የስራ ጉብኝት አድርጓል። ቡድኑ በባቡር ማጓጓዣ ዘርፍ የረጅም ዓመት የስራ ልምድ ያለውን የጀርመኑ ዶቼ ባንን አጠቃላይ የስራ ክንውን ተመልክቷል። ቡድኑ የኩባንያውን የባቡር ማምረቻ እና መጠገኛ ክፍሎችም ተዘዋውሮ ጎብኝቷል።
Published 08/28/19